Enter your keyword

About ETN

WELCOME TO ETN

Sharing the Love of Chirst to the Nation

ETN is a non-profit organisation and is funded by donations and gifts from peoole just like you. If you would like to join with us in spreading the good news, we would love to work with you towards that goal. The unprecedented growth of the church in Ethiopia has made it imperative to provide them with solid biblical teaching in their mother tongue. ETN produces 24/7 television program that provides solid teaching and trains Christians to reach out to their countrymen.

አሃዱ ...

ቀኑንና ሰአቱን አስታውሼ መናገር ባልችልም የቴሌቪዥን አገልግሎት የሚል የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ፓስተር አበራ የመጣው እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ ም እንደሆነ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ይናገራል ብሎ የሚገምት ማንም ባልነበረበት በዛ ወቅት የሞኝነት አለያም የእብደት የሚመስል ድምፅ ነበር፡፡ በወቅቱ እኔና ፓስተር እጮኛሞች ስለነበርን ይህንን የሰማውን ድምፅ ለእኔም ሆነ በወቅቱ በምናመልክበት ቤተክርስቲያን ለነበሩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሲናገር ያበደ ነበር የመሰለን፡፡ 1992 ዓ.ም. የሚያልፍበት መንፈሳዊ ውጊያ ስለነበረ ለፓስተር በጣም አስቸጋሪ ዓመት ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ቴሌቪዥን አገልግሎት ይናገራል ብሎ መገመት በጣም አስቸጋሪ ነበር። በርግጥም አበራ ሊያብድ ነው ወደሚለው ሃሳብ የተመጣው ከሁለት ነገሮች አንፃር ነበር፡- 1. የመንፈሳዊ ቴሌቪዥን አገልግሎት ለእኛ ለኢትዩጵያውያኖች በወቅቱ የማይመስል ህልም ስለነበረ፤ 2. ፓስተር ከነበረበት መንፈሣዊ ውጊያ፤ ከዚህም የተነሣ ማንም ለሃሣቡ ወይንም ለመጣው ድምፅ ፊት የሰጠው አልነበረም፡፡ ስለሆነም በወቅቱ የመጣው የእግዚአብሔር ድምፅ ለተወሰኑ አመታት ፋይሉ ተዘግቶ መቀመጥ ነበረበት፡ የአምላካችን የእግዚአብሔር ድንቅ አሰራር በዘመናት ሁሉ ያለማቋረጥ እየረዳን አሁን ላለንበት ዘመን አድርሶናል፡፡ ቃሉ ሁሉንም በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው እንደሚል በእርግጥም የእግዚአብሔር ጊዜ ሲመጣ የተናገረውን ሊፈፅም ማንም ሊከለክለው እንደማይችል በህይወታችን ያየነውና የተረዳነው እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔር ጊዜ ደረሰና እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ላይ የእግዚአብሔር ድምፅ ከመጣ ከ15 ዓመታት በኃላ በሳምንት አንድ ጊዜ ለ28 ደቂቃ የሚቆይ በአውሮፓ ለሚኖሩ ኢትዩጵያውንና ኤርትራውያን የሚተላለፍ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚል የቴሌቪዥን አገልግሎት በጀነሲስ ቻናል (Genesis Channel) አሀዱ ተብሎ ተጀመረ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር አምላካችን ይሁን፡፡

የራዕዩ ባለቤት እግዚአብሔር፣ የራዕዩ ተቀባይ ፓስተር አበራ፤ እግዚአብሔር በሰጠኝ ፀጋና እውቀት ራዕዩን እንዳካሂድ አኔን አስገብቶ በሦስት የተገመደ ገመድ እንደማይበጠስ አገልግሎቱ በእግዚአብሔር መሪነት ተጀመረ፡ ፡ በውስጣችን የነበረው ሀሴት ይህ ነው ተብሎ አይገለፅም፡፡ አገልግሎቱ እንደሚጀምር እርግጠኛ ስንሆን ወደ ፓስተር አበራ አንድ ሃሣብ መጣና ያንን ሃሣብ ይዞ ወደ ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና፣ ፓስተር ሐንፍሬ አሊጋዝ፣ ሐዋርያው ዳንኤል መኮንንና እንዲሁም በጣም ለምንወዳቸው ጓደኞቻችንና በብዙ ከዚህ አገልግሎት ጋር ወደቆመው ወንጌላዊ መስፍን ሸለመ በመሄድ ሃሳቡን አካፈላቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ከአራቱም አገልጋዩች የመጣው ምላሽ እግዚአብሔርን በብዙ እንድናከብረው አድርጎናል፡፡  ዶ/ር ቶሎሳ ፡- እግዚአብሔር ይናገር እንጂ  ፓስተር ሐንፍሬ፡- በጣም ደስ ይለኛል ለዘመናት ስጠብቀው የነበረ ጉዳይ  ሐዋርያው ዳንኤል፡- እግዚአብሔር ማንን ያስነሳ ይሆን የሚለውን የጥያቄ መልስ ማግኘቱን  ወንጌላዊ መስፍን፡- እንኳን እግዚአብሔር ተናገረህ እኔን ተናግሮ ቢሆን ኖሮ አገልግሎቱ አድካሚ፣ ብዙ ገንዘብ የሚጠይቅ፣ ከሰው የሚመጡት ተቃራኒ ቃላት ከባድ ቢሆኑም የተናገረው ጌታ ግን በአንድ ወር ተኩል ውስጥ ከግማሽ ሰዓት የአየር ሰአት ስርጭት ወደ አንድ ሰአት ተኩል አሻገረው፡፡ በዚህ ጊዜ ከነበርንበት ጀነሲስ ጣቢያ (Genesis Channel) ወደ ወንደርፋል ጣቢያ /Wondeful Channel/ የተሸጋገርን ቢሆንም አሁንም ስርጭቱ በአውሮፓ ላይ ብቻ የተወሰነ ነበረ፡ ፡ በዚህ ሁኔታ ለ7 ወራት አገልግሎቱ የቀጠለ ሲሆን እግዚአብሔር ለየት ያለ ነገር ያደረገው ስርጭቱ ለግማሽ ሰአት ቀድሞ የተቀዳ ስብከትና ለአንድ ሰዓት የቀጥታ ስርጭት መሆኑ ነው፡ ፡ ለ7 ወር በዚህ መልኩ ካለገልን በኋላ አንድ አርብ ምሽት የቀጥታው ስርጭት እየተካሄደ እያለ ፓስተር ወደ ውስጥ ተጠርቶ ወንደርፋል ጣቢያ /Wondeful Channel/ ስርጭቱን ወደ አፍሪካ እንዳስፋፋ ተነገረው፡፡ ወዲያው አዲስ አበባ ለምናውቃቸው ቤተሰቦችና አፈወርቅ ለሚባል ቴክኒሺያን በመደወል ስርጭቱን እንዲፈልጉና እንዲከታተሉ ተነገራቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ስሙ ይባረክ አገልግሎቱ በእርግጥ አገራችን ላይ እየተሰራጨ እንደሆነ መልካም ዜና ሰማን፡፡

በዚህ ግዜ ነበር ፓስተር አበራ ወደ ኢትዩጵያ በመሄድ ጥሪ ላቀረብንላቸው አገልጋዮች ራዕዩን ያካፈለው፡፡ ያን ግዜ ነው ከብዙዎች እግዚአብሔር የቴሌቪዥን ስርጭት በአገራችን እንደሚጀመር በተደጋጋሚ እንደተናገረ የሰማነው፡፡ እንዲሁም ከየት እንደሆነ በማይታወቅና በማይገመት ሰው አገልግሎቱ እንደሚጀምር እግዚአብሔር የተናገረውን መልእክት ለመስማት የቻልነው፡፡ እርግጥ ነው እግዚአብሔር በማንና በምን እንደሚሰራ በሚገባ መንገድ አንድን ይህንን ይሰራል ተብሎ የማይገመትን ሰው ከኢንግላንድ /England/ ምድር ተጠቅሞ የአገልግሎቱ ጅማሬ እንዲሆን አደረገው፡፡ ይኼ በመሆኑ ክብር ምስጋና ለአምላካችን ይድረሰው፡፡ ይህ ጅማሬ የእግዚአብሔር የራሱ መሆኑን የምንረዳው ገንዘብ፣ አቅም፣ የትምህርት ደረጃና የተለያዩ ነገሮች የሌለውን ሰው መርጦ ለክብሩ የሆነውን አገልግሎት መጀመሩ ሲሆን በሁሉም ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር እንጂ የማንም እጅ እንደለሌለበት ለመረዳት አያዳግትም፡፡ በስብሰባው ላይ ከተጠሩትና መላው ራዕዩን ከተካፈሉት አገልጋዩች መካከል የእግዚአብሔር ሰው ቶማስ ምትኩ እና ፓስተር አቢ እምሻው ወዲያውኑ ነው በአገልግሎቱ ለመጠቀም ፈቃዳቸውን የሰጡት፡፡ ፓስተር አበራ የመጀመሪያውን ስብሰባ አድርጎ ወደ ለንደን ከተመለሰ በኋላ ወንደርፋል ጣቢያ ጋር በመነጋገር በሳምንት አንድ ሰዓት ተኩል የነበረውን ስርጭት በቀን ሁለት ሰዓት በማድረግ አገልግሎቱን የቀጠለ ሲሆን ይህ የሁለት ሰዓት አገልግሎት ያለማቋረጥ ለአራት ወራት በብዙ ዋጋ እንዲቀጥል ሆኗል፡፡ ይህ በቀን የሁለት ሰአት አገልግሎት ሲሰጥ የተለያዩ አገልጋዩች ያስተማሩትን ትምህርት ወደ ለንደን /London/ በመላክ የኤዲንቲግ ስራውን እኛው እራሳችን እየሰራንና የአየር ሰአት ክፍያ ሳናስከፍል ነበር አገልግሎቱ ለ4 ወር ያክል ሲተላለፍ የቆየው። ከአራት ወር በኋላ ግን ከወንደርፋል ጣቢያ ከእኛ በሚያገኘው 5000 የእንግሊዝ ፓውንድ የወር ክፍያ ብቻ የ 24 ሰአት ስርጭቱን ወደ አፍሪካ መቀጠል ስላልቻለ አገልግሎቱ ተመልሶ በሳምንት ወደ አንድ ሰአት ተኩል ተቀነሰ፡፡ የተጀመረው አገልግሎት በብዙ አቅጣጫ መልካም መሆኑን ስለተረዳንና የምንሰማቸው ምስክርነቶች አገልግሎቱ በአንድ ሰዓት ተኩል ተወስኖ መቅረት እንደሌለበት ማረጋገጫ ስለሆኑልን ከወንደርፉል ጣቢያ ሌላ ስርጭቱን ወደ አፍሪካ የሚያደርስልን ሌላ ጣቢያ መፈለግ ግድ ሆነብን። ከዚህም የተነሳ በኦሜጋ፣ በዴያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክና በፌይዝ ጣቢያዎች ላይ ከ 2008 እስከ ሰኔ 2011 ድረስ አገልግሎቱ በቀን ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ሰባት ሰዓት ሲሰጥ ቆይቶአል። በፌይዝ ጣቢያ በቆየንባቸው ረዘም ያሉ ወራቶች ብዙ ተግዳሮቶች ያጋጥመን የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የጠራንና የታመነው አምላክ ባለ ብዙ ምህረት ስለሆነ ተግዳሮቶቹ በሙሉ በመልካም እየተቀየሩ ሲሄዱ አይተናል። እንዲያውም አገልግሎቱ ወደ 24 ሰዓት እንዲለወጥና ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ኔትወርክ ተብሎ እራሱን የቻለ ቻናል ሆኖ እንዲወጣ የሆነው ከእነዚህ ተግዳሮቶች አንዱ በመከሰቱ ነው። በየካቲት 2011 ዓም አንድ አርብ ምሽት የቀጥታ ስርጭት እያገለገልን እያለን ወደ ውስጥ ተጠርቼ ስርጭቱ አፍሪካ ላይ እንደተቋረጠ ነገሩኝ። የፓስተርን መንፈስ መረበሽ ስላልፈለኩኝ በውስጡ የነበረው መልዕክት እስኪጨርስ ዝም አልነውና መጨረሻ ላይ ነገርነው። በጣም የገረመንና እስካሁንም ድረስ የሚገርመን በልባችን ውስጥ የገባው የእግዚአብሔር ሰላምና መረጋጋት ነው። አርብ ምሽት ስለነበር የጣቢያውን ባለቤቶች አግኝተን መነጋገር አልቻልንም ነበርና ለሰኞ ቀጠሮ እስክንይዝ ድረስ እዛው ስቱዲዮ ውስጥ ቁጭ ብለን የጌታን ሃሳብ መጠየቅ ጀመርን።

ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው!

ከስቱዲዮው ሳንወጣ ጌታ ቃሉን ሰጠን። ያንን ቃል ይዘን ሁልጊዜ አርብ ምሽት በቤታችን ጸሎት ይደረግ ስለነበር በምስጋና ተሞልተን ወደ ጸሎቱ ተቀላቀልን። እግዚአብሔር መልካም ነገርን ከዚህ ሁኔታ ውስጥ እንደሚያወጣ አመነው።ሰኞ መጣና ወደ ፌይዝ ስቱዲዮ አቀናን። ከጣቢያው ስራ አስኪያጆች ጋር ቁጭ ብለን ስንነጋገር ስርጭቱ የተቋረጠው ብዙ ያልተከፈለ ገንዘብ ስለነበረ እንደሆነ ገለጹልን። የገንዘብ አቅም ስለሌላቸው በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል እንደማይችሉ ገለጹልን። በዚህ መሃል ፓስተር አበራ ምንአልባት የ24ቱን ሰዓት ለሁለት ተካፍለን ስርጭቱ እንዲቀጥል የሚል ሃሳብ ሲያቀርብ ወደዚህ ሃሳብ ከመድረሳችን በፊት ያለብንን እዳ መክፈል አለብን፤ እዳውን ካልከፈልን ስርጭቱ እንደማይቀጥል ተነግሮናል። እኛ ደግሞ በዚህ ሰዓት ያለብንን እዳ መክፈል አንችልም አሉን። እኔም ሆንኩ ፓስተር አበራ በውስጣችን ስርጭቱ በፍጹም መቋረጥ የለበትም ብለን ስላመንን የእኛ ያልሆነውን ዕዳ የተወሰነውን ያክል ለመክፈል ተስማማን። ይህንንም ሃሳብ ሳተላይቱን ላከራዩን ሰዎች ለመንገር ለሮብ ቀጠሮ ይዘን ተለያየን። የቀጠሮው ቀን ደረሰና ሃሳባችንን ለሳተላይት አከራዮቹ ነገርናቸው። ኤልሻዳይ ቲቪ 20.000 የአሜሪካ ዶላር ሊከፍልና የተቀረውን 45.000 ዶላር ፌይዝ ጣቢያ ሊከፍል እኛም የምንከፍለውን ክፍያ በፊት እንደምናደርገው የፌይዝ ጣቢያ የሂሳብ ቁጥር ውስጥ ልንጨምር ተስማምተን ጣቢያው እንደገና ስርጭቱን እንዲጀምር ተደርጎ ተለያየን።

ቀኑንና ሰአቱን አስታውሼ መናገር ባልችልም የቴሌቪዥን አገልግሎት የሚል የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ፓስተር አበራ የመጣው እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ ም እንደሆነ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ይናገራል ብሎ የሚገምት ማንም ባልነበረበት በዛ ወቅት የሞኝነት አለያም የእብደት የሚመስል ድምፅ ነበር፡፡ በወቅቱ እኔና ፓስተር እጮኛሞች ስለነበርን ይህንን የሰማውን ድምፅ ለእኔም ሆነ በወቅቱ በምናመልክበት ቤተክርስቲያን ለነበሩ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሲናገር ያበደ ነበር የመሰለን፡፡ 1992 ዓ.ም. የሚያልፍበት መንፈሳዊ ውጊያ ስለነበረ ለፓስተር በጣም አስቸጋሪ ዓመት ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር ስለ ቴሌቪዥን አገልግሎት ይናገራል ብሎ መገመት በጣም አስቸጋሪ ነበር። በርግጥም አበራ ሊያብድ ነው ወደሚለው ሃሳብ የተመጣው ከሁለት ነገሮች አንፃር ነበር፡- 1. የመንፈሳዊ ቴሌቪዥን አገልግሎት ለእኛ ለኢትዩጵያውያኖች በወቅቱ የማይመስል ህልም ስለነበረ፤ 2. ፓስተር ከነበረበት መንፈሣዊ ውጊያ፤ ከዚህም የተነሣ ማንም ለሃሣቡ ወይንም ለመጣው ድምፅ ፊት የሰጠው አልነበረም፡፡ ስለሆነም በወቅቱ የመጣው የእግዚአብሔር ድምፅ ለተወሰኑ አመታት ፋይሉ ተዘግቶ መቀመጥ ነበረበት፡ የአምላካችን የእግዚአብሔር ድንቅ አሰራር በዘመናት ሁሉ ያለማቋረጥ እየረዳን አሁን ላለንበት ዘመን አድርሶናል፡፡ ቃሉ ሁሉንም በጊዜው ውብ አድርጎ ሰራው እንደሚል በእርግጥም የእግዚአብሔር ጊዜ ሲመጣ የተናገረውን ሊፈፅም ማንም ሊከለክለው እንደማይችል በህይወታችን ያየነውና የተረዳነው እውነታ ነው፡፡ ስለዚህም የእግዚአብሔር ጊዜ ደረሰና እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ላይ የእግዚአብሔር ድምፅ ከመጣ ከ15 ዓመታት በኃላ በሳምንት አንድ ጊዜ ለ28 ደቂቃ የሚቆይ በአውሮፓ ለሚኖሩ ኢትዩጵያውንና ኤርትራውያን የሚተላለፍ እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚል የቴሌቪዥን አገልግሎት በጀነሲስ ቻናል (Genesis Channel) አሀዱ ተብሎ ተጀመረ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር አምላካችን ይሁን፡፡

እዚህ ጋር ለአንባቢዎቻችን ልናሳውቅ የምንፈልገው 20.000 ዶላር ለመክፈል ስናስብ የራሳችን የሆነ ያስቀመጥነው ገንዘብ ወይንም ደግሞ ሚኒስትሪው አካውንት ውስጥ የተጠራቀመ ገንዘብ ኖሮ አልነበረም። ከዚህ ቀደም ወንደርፉል ጣቢያ ላይ እያለን የብዙ አገልጋዮች ፕሮግራም ያለምንም የገንዘብ ክፍያ ይተላለፍ ስለነበር በእኛ ላይ የገንዘብ እጥረት ስላመጣብን ከባንክ 10.000 የእንግሊዝ ፓውንድ ተበድረን ስለነበር የፌይዝን ጣቢያ እዳ ለመክፈል ስንስማማ እንደገና ወደ ባንክ ሄደን ብድር ለመጠየቅ ድፍረት አልነበረንም። ነገር ግን ለዚህ ክፍያ የሚሆን ከግለሰብ ገንዘቡን ተበድረን ወደ ፌይዝ ጣቢያ የሂሳብ ቁጥር ውስጥ አስገባን። በጣም የሚያሳዝነው ግን ወደ ፌይዝ ጣቢያ ያስገባነው ገንዘብ ለሳተላይት አከራዮቹ ሳይከፈል በመቅረቱና ገንዘቡን ለሌላ ጉዳይ ከማዋላቸው የተነሳ እንደገና ሌላ ችግር ተፈጠረ። በዚህን ወቅት ከፌይዝ ጣቢያ ጋር ያለንን ግንኙነት ማቋረጥ እንዳለብንና ወደ ሳተላይት አከራዮቹ በመሄድ መወያየት እንዳለብን ተረዳን። ባደረግነውም ውይይት እኛ የወሩን ክፍያ በራሳችን መክፈል ከቻልን ሙሉ ጣቢያ እንደሚሰጡን ገለጹልን። ይህንን ስናውቅ እስከዚህ ቀን ድረስ የረዳን አምላክ አሁንም ይረዳናል በማለት ከሃሳቡ ጋር በመስማማት እ.አ.አ በሰኔ ወር 2011 ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ኔትወርክ የመጀመርያው የኢትዮጵያውያን የ24 ሰአት የክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ በመሆን አገልግሎቱን በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሃገሮች ሁሉ ስርጭቱን ጀመረ። በዚያ ጊዜ የነበረን ደስታ ይህ ነው ተብሎ አይነገርም። ስርጭቱ በብዙ ውጣ ውረድ ነገር ግን ቀን በቀን እየተሻሻለ ለአንድ ዓመት ከሁለት ወር ያለማቋረጥ ቀጠለ። እ.አ.አ በ ሚያዝያ 2012 ፓስተር አበራ በሌላ አገልግሎት ወደ ዱባይ መሄድ ነበረበትና በዛ በነበረው ቆይታ በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ወገኖቻችንን የኤልሻዳይ ቲቪን መከታተል ቢጀምሩ ለመንፈሳዊው ህይወታቸው እድገት፣ በጌታ ላልሆኑ ደግሞ ወደ ጌታ መምጫ መንገድ እንደሚሆንላቸው ስለተረዳ ወዲያውኑ ከሶስት ወር በኋላ ስርጭቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ወደ ሰሜን አፍሪካ እንደሚሰራጭ የእምነትን ቃል ተናግሮ ወደ ለንደን ተመለሰ። ድንቅን ማድረግ ልማዱ የሆነው፣ በእምነት የተናገርነውን የሚያጸና ጌታ ፓስተር እንደተናገረው ሶስት ወሩ እንዳለቀ በሚያስደንቅ ሁኔታ በነሐሴ ወር 2012 ዓም የመካከለኛው ምስራቅ ስርጭት ተጀመረ። ሆኖም ግን ስርጭቱ በተጀመረ በአራተኛው ወር በነበረብን የገንዘብ እጥረት የመካከለኛውን ምስራቅ ስርጭት ልናቆም እንደሆነ በቀጥታ ስርጭታችን ላይ ለጌታ ሕዝብ አስታወቅን። በዚህ ጊዜ ከተለያየ ስፍራ የእግዚአብሔር ሕዝብ ልክ ቀፎው እንደተነካ ንብ ይህ አገልግሎት አይቆምም በማለት ድጋፉን ይሰጥ ጀመር። በተለይ በሳውድ አረቢያ የነበሩ ወገኖች በፓስተር ዴክሲ በኩል ያደረጉት ልገሳ የማይረሳ ነው። ጌታ በነገር ሁሉ ይባርካቸው። እግዚአብሔር አገልግሎቱ እንዲቀጥል ስለፈለገ በዓመት አንዴ ከሕዝባችን የገንዘብ ማሰባሰብ እንድናደርግ በልባችን አድርጎ የጌታ ሕዝብ በሚሰጠውና አገልጋዮች በሚከፍሉት አነስተኛ ክፍያ አገልግሎቱ እንዲቀጥል አደረግን። በዚህ አጋጣሚ በጥቂቱም ይሁን በብዙ ከእኛ ጋር በገንዘባቸው የቆሙትን ኢትዮጵያውያኖችና ኤርትራውያኖች እንዲሁም በአረብ አገር ላሉ ወገኖቻችን በሙሉ ጌታ ይባርካችሁ ለማለት እንወዳለን። ብዙዎች በቋሚነት አጋር በመሆን በየአመቱ አገልግሎቱን ይደግፋሉ። የእስራኤል አምላክ ይባርካችሁ። ያለፍንበትን መንገድ ስናስብ በጉዞአችን ከእኛ ጋር በአንድም በሌላም መንገድ አብረውን ዋጋ ለከፈሉ ወገኖቻችን ከዚህ እንደሚከተለው ለመባረክ እንወዳለን።